ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የምርጫ ቁሳቁስ ማጓጓዣ ችግር አፋጣኝ እልባት ካላገኘ አገር አቀፉን የምርጫ ሂደት ሊያስተጓጉል ይችላል ተባለ።
በዕጩዎች ምዝገባ፣ የመራጮች ምዝገባ መረጃ፣ የምርጫ ጣቢያ ዝግጅትና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ ያለውን ዝግጅት ለፓርቲዎቹ ገለጻ አድርጓል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሰፊ አገርና ህዝብ ነገር ግን የመንገድ መሰረት ልማት ውስንነት ያለበት አገር ላይ ምርጫን በአግባቡ ለማካሄድ መንግሥት ከፍተኛ እገዛ ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ከወዲሁ አሳስበዋል።
ሁሉንም የአገሪቱ አካባቢ ሊሸፍን የሚችል የትራንስፖርት አቅም ያለው መከላከያ ሠራዊት መሆኑን የጠቆሙት ሰብሳቢዋ፤ በትግራይ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በተፈጠረው ጫና እገዛው እንደተስተጓጎለና የማጓጓዣ ችግሩ አፋጣኝ እልባት ካልተሰጠው የምርጫ ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያቃውሰው እንደሚችል ገልጸዋል።
ምርጫ ቦርድ በመላ ሀገሪቷ 663 የምርጫ ክልሎችን ከፍቶ የምርጫ ቁሳቁሶችን እያጓጓዘ ሲሆን፤ በቀጣይም ለ50 ሺህ ምርጫ ጣቢያዎች እንደሚያሰራጭ ይፋ አድርጓል።