ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሀገሪቱ ግዙፍ የኢኮኖሚ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላዳ ታክሲዎችን ለመለወጥ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ፈቀደ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት የሰጡ ትናንሾቹን ሰማያዊ በነጭ ታክሲ ወይም በተለምዶ የላዳ ታክሲዎችን በአዲስ ለመተካት ለተያዘው ፕሮጀክት ትልቅ የተባለውን የድሰት ቢሊዮን ብር ብድር ማመቻቸቱን የገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ነው።
የአዲስ አበባ ላዳ ታክሲዎች ማህበር ኤላ ላውቶ ኢንጂነሪንግ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመሆን ጊዜ ያለፈባቸውን ላዳ ታክሲዎች በዘመናዊ መኪኖች ለመተካት በጋራ ለነደፉት ፕሮጀክት የሚውለው የብድር ገንዘብ ስምምነት በሸራተን ሆቴል የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ተከናውኗል።
የከተማዋ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጅነር ስጦታው አካለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሮጀክቱ ለከተማዋ አዋጭ መሆኑን በማመን ገንዘቡን በመፍቀዱ ምስጋና አቅርበዋል።
ኢንጂነሪንግ የሚያቀርባቸው 10 ሺኅ 500 ዘመናዊ መኪኖች ወጪ ሀያ በመቶው በባለ ንብረቶች የሚሸፈን ሲሆን ቀሪው 80 በመቶ ከባንክ በሚገኘው ብድር የሚከፈል መሆኑ ታውቋል።
የመጀመሪያዎቹ ዘመናዊ ታክሲዎች በአራት ወራት ውስጥ ለባለንብረቶቹ የሚደርሱ ሲሆን ወደ ፊትም በተመሳሳይ አሮጌ ታክሲዎቹን በአዲስ የመተካት ሥራ እንደሚካሄድ ከተማ አስተዳደሩ ጠቁሟል።