የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተናን በተያዘለት ጊዜ ለማከናወን የሚገድብ ነገር የለም

የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተናን በተያዘለት ጊዜ ለማከናወን የሚገድብ ነገር የለም

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት አድርጊያለሁ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ፈተናው በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲከናወን ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ሚኒስትሩ ሀገር ዐቀፍ ፈተናውን በተያዘለት የግዜ ገደብ ለመስጠት እና ለማጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል።
 ፈተናው በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ በከፍተኛ ጥንቃቄና ቅንጅት እየተሠራ ነው ያሉት የሀገር ዐቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦተሬ፤ ከየካቲት 21 እስከ 26 ቀን 2013 ድረስ የመፈተኛ ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ሥራ ይጠናቀቃል ብለዋል።

LEAVE A REPLY