ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በቀጣዮ ሀገራዊ ምርጫዎች የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምረጡኝ ቅስቀሳቸው በሚዲያ የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች ግጭትና ጥላቻ ቀስቃሽ እንዳይሆኑ ሊጠነቀቁ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ማኅበር አሳሰበ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን በሚያካሂዱት ቅስቀሳ የምርጫ መመሪያውን እንዲከተሉና የሰለጠነ የፖለቲካ ስልት እንዲያራምዱ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱዓለም አስጠንቅቀዋል።
በቀጣይ በሚደለደለው የአየር ሰዐት ፓርቲዎች በተለያዩ ጉዳዮች የያዟቸውን አማራጭ ፖሊሲዎች ለሕዝቡ በማስተላለፍ የተመደበላቸውን ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀሙም ማኅበሩ ከወዲሁ ማሰጠንቀቂያ ሰጥቷል።