ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የምሁራንን ተሳትፎ የሚያስተባብር ፎረም ለመመሰረት የሚያግዝ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተደራጅቷል ተባለ።
የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮሚቴዉ በህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጸሐፊነት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት፤ ዉሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ዩኒቨርስቲዎችን እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን አባላት በማድረግ መመሥረቱ እየተነገረ ነው።
በህዳሴዉ ግድብ ዙርያ ምሁራንን የሚያስተባብር አደረጃጀት እንዲፈጠር የረጅም ጊዜ ጥያቄዎች መኖራቸውን ተከትሎ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም ዩኒቨርስቲዎችን በማስተባበር በፎረሙ ምስረታ ሂደት ድጋፍ እንዳደረገ ከደረሰን ዜና መረዳት ተችሏል።