የትግራይ የተደራጁ ወጣቶች ሊሠሩ የነበረውን ሸፍጥ አልጀዚራ አጋለጠ

የትግራይ የተደራጁ ወጣቶች ሊሠሩ የነበረውን ሸፍጥ አልጀዚራ አጋለጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በስፍራው ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ለመገምገም ወደ ትግራይ ክልል የገባው አልጀዚራ አሁን ላይ ጦርነት እንደሌለ እና እንዳልተመለከት ዘገበ።

“በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር የምትገኘው የመቀለ ከተማዋን ተዟዙርን ባየንበት ጊዜ ምንም ጦርነት አላየንም። ለህዝቡ ህወሓት ወደየት ነው? ብለን ጠየቅናቸው። ህወሓት የለም ሸሽቶ እጎራ ስር ነው ያለው አሉን። ተልሰው ይመጣሉ ስንል ጠየቅናቸው እነርሱ ግን አናውቅም አሉን” በማለት የዘገበው  አልጀዚራ በዚህ ወቅት ትግራይ በአንጻራዊ ሰላም ላይ ትገኛለች ብሏል።
ህወሓት ለ27 አመት ኢትዮጵያን የመራና የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሁኔታ ጥንቃቆ የሚያውቅ በተንኮል ተወዳዳሪ የለለው ድርጅቱ ነው። ምናልባት አሁን ጫካ ሊሆን ይችላል እንጅ ወደፊት ምን ሊያመጣና ምን ሊያደርግ እንደሚችል አይታወቅም አለ።
.
በመቀሌ ቆይታችን ላይ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው መጠለያ ያሉ ሰዎችን አይተናል። ትንሽ የሚባል የምግብ አቅርቦት ችግር ቢኖርም የሀገሪቱ መንግስት ከእርዳታ ድርጀቶች ጋር በመሆን ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራ መሆን አረጋግጠናል ሲልም ዓለም ዐቀፍ ተቋሙ አልጀዚራ ዘግቧል።
 “ጦርነት ይኖር ይሆን ወይ ሰላም ይሰፍናል ወይ!” የሚለው ጥያቄ በመቀሌ ሕዝብ ውስጥ ይብሰለሰላል። ወደ መቀሌ እየገባን እያለ የተወሰኑ የተደራጁ የሚመስል ወጣቶች አልጀዚራ ሚዲያ መሆኑን ሲያውቁ ተገደልን፣ ተደፈርን፣ ተረሸንን፣ ተጨቁነናል አሉ። ሁኔታቸውን ስንመለከት ከውስጣቸው እጃቸውን እንዲያጣምሩና “ተገደልን ተደበደብን ተደፈርን” እንዲሉ የሚያዛቸው ሰው መኖሩን ስናይ ነገሩ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ መሆኑን አመነን” ያለው አልጀዚራ ህወሓት በቅሪተ አካሎቹ ሊፈጽም የነበረውን ሸፍጥ አጋልጧል።

LEAVE A REPLY