ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት አንድ ቢሊየን 200 ሚሊየን ብር ለሚያካሄደው የተቀናጀ የልማት ፕሮግራም ከሲዳማና ደቡብ ክልሎች ጋር ስምምነት መፈራረሙ ተሰማ።
በደቡብ ክልል ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ለሚካሄደው የልማት ፕሮግራም ስምምነት የተፈራረሙት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ አያሌው ዝና ሲሆኑ የሲዳማ ክልልን በመወከል ደግሞ የ69 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ስምምነት የተፈራረሙት ደግሞ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሶ ገረመው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በስምምነቱ በደቡብ ክልል ሥድሥት ዞኖችና 12 ወረዳዎች ተግባራዊ በሚደረገው ፕሮግራም 2 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ፣ በሲዳማ ክልል ሁላ ወረዳ ደግሞ ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።