ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከወርሐ መስከረም ጀምሮ ተደጋሚ ጥቃት ሲሰነዘርበት የቆየው ኦነግ ሸኔ በምስራቅ ወለጋ ነዋሪዎችን መግደሉ ተሰማ።
ሀሙስ ዕኩለ ቀን የኦነግ ሼኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አስራ አንድ ሰዎች ሲገደሉ ከሀያ በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ የዘገበው ዋዜማ ራዲዮ ነው።
የኦሮሚያ ልዮ ኃይል የምስራቅ ወለጋ እና የምዕራብ ወለጋ ነዋሪዎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ማስገደዱንና በዚህ ውሳኔ ነዋሪዎች ደህንነታቸው ስጋት ላይ መውደቁን መግለጻቸውን ኢትዮጵያ ነገ ቀደም ሲል መዘገቡ አይዘነጋም።