200 ሰዎች ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

200 ሰዎች ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ከኤርትራ ወታደሮች እና ከአማራ ልዮ ኃይል ጋር በተያያዘ አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግሥት በድጋሚ ማስጠንቀቂያ ሰጠች።

አምንስቲ ኢንተርናሽናል በአክሱም ከተማ አርብ በተገደሉት ሰዎች አሟሟት ላይ የኤርትራ ወታደሮች እጅ እንዳለበት መግለጹን ተከትሎ ቀደም ሲል የዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮችን ከትግራይ እንዲያስወጣ ያሳሰበችው አሜሪካ ዳግመኛ ጥያቄ አቅርባለች።
 የአማራ ልዩ ኃይል የፈደራሉ ሠራዊት ከህወሓት ኃይሎች ጋር ወታደራዊ ግጭት ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሆን ተሳታፊ እንደነበር የሚያስታውሰው የአሜሪካ መንግሥት መግለጫ፤ ይህ የክልል ልዮ ኃይልም በአስቸኳይ የትግራይን ክልል ለቅቆ ሊወጣ ይገባል ብሏል።
 ዓለም ዐቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከ200 በላይ ሰዎች በአክሱም ከተማ በኤርትራ ወታደሮች ተገድለዋል የሚል ሪፖርት ማውጣቱን የመንግሥታቸውን መግለጫ ይፋ ያደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሓላፊ አንቶኒ ቢልንከን፤ “በተለያዩ ወገኖች የሚፈጸሙት ግድያዎች፣ በኃይል ማፈናቀልን፣ ጾታዊ ጥቆቶች እንዲሁም ሌሎች አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጥብቀን እናወግዛለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY