ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– 354 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከአስከፊው የቤይሩት እስር ቤት ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸው ተነገረ።
ኤልማ የተባለ ድርጅት ከፍሪደም ፈንድ እና የኢ.ፌዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ከሊባኖስ ቤይሩት ከተማ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ከዜናው መረዳት ችለናል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን መንግሥት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቀጣይም ሌሎች ስደተኞችን ወደ ሀገር ቤት ለማምጣት ማቀዱ ተሰምቷል።