ኦፌኮ በቀጣዮ ሀገራዊ ምርጫ እንደማይሳተፍ ይፋ አደረገ

ኦፌኮ በቀጣዮ ሀገራዊ ምርጫ እንደማይሳተፍ ይፋ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በወርሃ ግንቦት ይካሄዳል በሚባለው ሀገራዊ ምርጫ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) እንደማይሳተፍ ገለጸ።

ፓርቲያችን ያለ ፍላጎቱ በመንግሥት ተገፍቶ ከምርጫው ለመውጣት ተገዷል ያሉት የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያወጣቸው በነበሩ መግለጫዎች የታሰሩ አመራሮቹ እንዲፈቱ፣ በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች የተዘጉ ቢሮዎቻቸው እንዲከፈቱ፣ እንዲሁም ታማኝነት ያለው ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አገራዊ ምክክር እንዲደረግ መጠየቁንም አስታውሰዋል።
ባለፈው ሳምንት ከምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ጋር ፖለቲካ ፓርቲዎች የዕጩ ምዝገባን በተመለከተ በተደረገ ውይይት ላይ መሳተፋቸውን የተናገሩት አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ ኦፌኮ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ ዕጩ እያስመዘገበ እንዳልሆነ እና ማስመዝገብም እንደማይችል፣ ስለዚህም ምርጫው ላይ መሳተፍ እንደማይችል ለምርጫ ቦርድ ገልጿል ብለዋል።
ኦፌኮ እስካሁን ድረስ ቢሮዎቻቸው በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ተዘግተዋል ያሉት የፓርቲው አመራር፤ ከዋናው የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምርጫውን እንዲያስፈጽሙ ከተመደቡ አምስት ሰዎች አራቱ እስር ቤት እንደሚገኙ አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY