የኤርትራ ወታደሮች ትግራይን ለቀው እንዲወጡ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሙሉ ድምፅ ተስማማ

የኤርትራ ወታደሮች ትግራይን ለቀው እንዲወጡ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሙሉ ድምፅ ተስማማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በመቀለ እና የተለያዮ የትግራይ አካባቢዎች የሚገኘው የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ ክልል እንዲወጣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አንድ አይነት አቋም መያዙን የአስተዳደሩ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ መኖራቸውን ሕዝቡ በዐይኑ ያየው ሀቅ ነው ያሉት የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራር አባል፤ ይህን በተመለከተ አስተዳደሩ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይን ለቀው እንዲወጡ አንድ አቋም ይዟል ብለዋል።
ሰሞኑን የአሜሪካ መንግሥትን ጨምሮ የተለያዮ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት የኤርትራ ወታደሮችን ፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ በአስቸኳይ እንዲወጣ ማሳሰቡ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY