ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ፎርብስ በሪፖርቱ ይዞት እንደወጣው መሪ ከሆነም በ2021 የአፍሪካ ባለብቶችን ወይም ቢልየነሮችን ስም ዝርዝር ይፋ አደርጓል።
በተገኘው ዝርዝር መረጃ መሠረት ናይጄሪው ባለሃብት አልኮ ዳንጎቴ የመጀሪያ ደረጃውን ሲይዝ፣ የግብጹ እና የደቡብ አፍሪካው ናሲፍ ሳዊሪስ እና ሊኪ ሃፑንሃይመር የሁለተኛ ደረጃ እንደያዙ አስታውቋል።
የደቡብ አፍሪካዎቹ ዮሃን ይፐርት እና ማይክ አንዱንጋ የአራተኛነት እና የአምስተኝነት ደረጃን ይዘዋል። በተመሳሳይ ናይጄሪያዊው አብዱል ሰመድ ራቢዮ ስድስተኛ ደረጃን መያዛቸው ታውቋል።
ኢሳድ ሪብራብ ከአልጄሪያ፣ ናጊብ ሳዊረስ ከግብፅ፣ ፓትሪስ ሞሰቤ እና ሞደስፔር ከደቡብ አፍሪካ ከሠባተኛ እስከ ዐሥረኛ ደረጃ መያዛቸውን ፎርብስ መጽሔት አረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም በአፍሪካ የሀብታሞች ደረጃ ውስጥ ተካትተው የነበሩት ሼህ ሞሐመድ አል አሙዲን ከፍተኛ ሀብታቸው በሳዑዲ መንግሥት መወረሱን ተከትሎ በዐሥሩ ሀብታሞች ውስጥ መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል።