ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ በ2030 HIVን ሙሉ ለሙሉ የመግታት ውጥን እንዳላት ፤ ቫይረሱ የሚገታውም በሦስት ዜሮዎች ህግ እንደሆነ ተገለጸ።
የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት HIVን ለመከላከል ተቋማትና ክልሎች መከወን ያለባቸውን ስራ ለማስተዋወቅ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው ይህ ውጥን ይፋ የተደረገው።
የጤና ሚኒስቴር የ HIV ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ምርቴ ጌታቸው፤ ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር በ2030 ሦስቱን የዜሮ ሕጎች በመጠቀም ማለትም፤ “ዜሮ በአዲስ የመያዝ ምጣኔን በአዲስ ምክንያት የሚከሰት ሞትን ዜሮ በማድረግ እና ዜሮ አድሎና መገለልን ተግባራዊ በማድረግ HIVን ለመግታት ውጥን ተይዟል” ብለዋል።