ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ በተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ዋና ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆኑ

ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ በተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ዋና ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆኑ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና  ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲወዳደሩ ብቸኛው አፍሪካዊ እጩ በማድረግ በሙሉ ድምጽ መምረጡን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ገለጸ።

ዶ/ር አርከበ ባለፉት ሠላሣ አመታት ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትና ቀጣይነት ላለው ሁሉን አቀፍ መዋቅራዊ ሽግግር የሚያግዙ ፖሊሲዎችን በማውጣት እና በማስተግበር ስኬታማ እንደሆኑ አረጋግጫለሁ ሲል ሕብረቱ አስታውቋል።
የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅቱ በብቁ ዋና ዳይሬክተር መመራት እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተው መወያየታቸውን ተከትሎ፤ የሕብረቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባካሄደው ውይይት፣ ዶ/ር አርከበ ካላቸው የስራ ልምድ አኳያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በመስኩ ተጨባጭ ለውጥ እንደሚያመጡ ባለሙሉ እምነት በመሆናቸው እጩነቱን አጽድቀውታል።

LEAVE A REPLY