ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ለ39 ቀናት የረሃብ አድማ ላይ የቆዩት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነ በአትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ሱፐር ኢንቴንደንት ሁሴን ሸቦ ሸምጋይነት የረሃብ አድማቸውን ለማቆም መስማማታቸው ይፋ ሆኗል።
እነ አቶ ጃዋር የረሃብ አድማቸውን ለማቆም የተስማሙት “ያነሷቸው ጥያቄዎች ተመልሰው ሳይሆን በአገር ሽማግሌዎች ተማጽኖና ጫና” መሆኑም ተነግሯል።
ይሁንና በረሀብ አድማው ዙሪያ የተለያየ ሀሳብ ከበርካታ ወገኖች መሰንዘሩ አልቀረም። ከሁሉም ጎልቶ የወጣው ሀሳብም “እንዴት ሰው ለ39 ቀናት ያለምግብ ሊቆይ ይችላል?” የሚል መሆኑ ተስተውሏል።
__________________________
ኢትዮጵያ ነገ ይህንኑ መነሻ አድርጋ ተከታዩን 10 ዓመታት የወሰደ የአለማችን ረጅሙ የረሃብ አድማን ልታስታውሳችሁ ትወዳለች:-
ህንዳዊቷ አይሮም ቻኑ ሳፑላ በመላው ዓለም iron lady of samilla እየተባለች የምትደነቅና የምንጊዜውም ረጅም የረሃብ አድማ ያደረገች አስገራሚ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ናት።
የህንድ ወታደሮች መሳሪያ ባልታጠቁ ንፁሃን መብት ጠያቂዎች ላይ የወሰደውን የሃይል እርምጃ በመቃወም ለ500 ሳምንታት እህል ውሃ ወደአፏ ሳታስጠጋ ድርጊቱን ስታወግዝ ቆይታለች። አድማዋ በአለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ ዕውቅና ከማግኘቱም ባሻገር በህንድ መንግስት ላይ ከባድ ጫና እንዲደርስና በሀገሪቱ የስርዓት ለውጥ እንዲፈጠር አስችላለች። በዚህ ታላቅ ተግባሯም ከ”asian human rights commission” ያገኘችውን የህይወት ዘመን ሽልማት ጨምሮ በርካታ አዋርዶችን አግኝታለች።