የአማራና ትግራይ ክልሎች ፍጥጫ ወደ “ደም መፋሰስ” እንዳይሻገር ተሰግቷል!

የአማራና ትግራይ ክልሎች ፍጥጫ ወደ “ደም መፋሰስ” እንዳይሻገር ተሰግቷል!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአማራ ክልላዊ መንግስትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የወልቃይትና የራያ አካባቢዎችን በተመለከተ በየፊናቸው የሚሰጡት የተናጠል መግለጫ ክልሎቹን ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራቸው ስጋት ፈጥሯል።

ሰሞኑን በሁለቱም የየክልል ባለስልጣናት በኩል እየታየ ያለው የቃላት ጦርነትም ፍጥጫው ወደ አሳሳቢ ደረጃ እየተሻገረ ለመሆኑ ማሳያ ነው ተብሏል።

በአማራ ክልልና በትግራይ ክልል አስተዳደሮች እየተሰጡ ያሉ የተናጠል መግለጫዎች እርስ በርስ በመወነጃጀል ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው በክልል አስተዳደሮቹ መካከል የሚታየውን ውጥረት ይበልጥ እያባባሰው ስለመሆኑ የጠቀሱ ታዛቢዎች፣ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በክልሎቹ መካከል ደም አፋሳሽ ግጭት ሊከሰት እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY