ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ በህንዱ ሴረም ኢንስቲትዩት የተመረቱ የአስትራ ዜኔካ ክትባቶችን የተቀበለች ሲሆን፣ ብዛታቸውም 2.2 ሚሊዮን መሆኑ ተገልጿል።
ይሁንና ከክትባቶቹ ጋር በተያያዘ በህብረተሰቡ ውስጥ የተሠራጨው “ያልተጨበጠ መረጃ” በክትባት ዘመቻው ላይ መሰናክል እንዳይፈጥር ስጋት ጭሯል። “ኮሮና በአለም ላይ የተከሰተው ምዕራባውያኑ ሆነ ብለው ባቀነባበሩት ሴራ ነው።
ክትባቱም የሰውን ልጅ ለመቆጣጠርና ለክፉ መንፈስ አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው” የሚል ወሬ ከወራት በፊት ጀምሮ ይፋዊ ባልሆነ መልኩ ሲሰራጭ መቆየቱን ያመለከቱ የመረጃ ምንጮች፣ የኮሮና ክትባት ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ደግሞ እነዚህ “አጉል አመለካከቶች” በስፋት እየተንፀባረቁና “አልከተብም” የሚሉ ዜጎችም ቁጥራቸው እየተበራከተ እንደሚገኝ አመልክተዋል። እንደ ጤና ሚንስትር መግለጫ፣ ክትባቶቹ ቫይረሱን በመዋጋት ረገድ ግንባር ቀደም ናቸው ለተባሉ የህክምና ባለሙያዎች እና ሌሎችም በቅድሚያ የሚሰጡ ይሆናል።