ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– 6ኛው አገራዊ ምርጫ ሊካሄድ የወራት ዕድሜ በቀሩትና የምርጫ ዝግጅቶች እየተገባዱ ባሉበት ወቅት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ጥያቄው በሂደት ላይ መሆኑን እና መንግስት ምላሽ ሲሰጥ በይፋ የሚለቁ መሆኑን ከቀናት በፊት የገለፁ ሲሆን፣ የሚመሩት ባለስልጣን መ/ቤት ለመጪው ምርጫ ሰላማዊና ፍትሃዊ መሆን፣ ሚዲያዎችን በመቆጣጠር በኩል ያለው ድርሻ ወሳኝና ከባድ መሆኑ እየታወቀ በዚህ ወቅት መልቀቂያ ማስገባታቸው ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኘሬዝዳንቷ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ “ቦርዱ በምርጫ ወቅት ከዚህ ቀደም ሲያደርገው ከነበረው በበለጠ መልኩ ሚዲያዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል” ብለዋል።