በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት መንግሰትና አከፋፋዮች እየተካሱ ነው

በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት መንግሰትና አከፋፋዮች እየተካሱ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ ሁሉም ከተሞች ለተከሰተው የነዳጅ እጥረት መንግስት ነዳጅ አቅራቢዎችን በምክንያትነት ሲጠቅስ፣ ነዳጅ አቅራቢዎችም ጥፋተኛው መንግስት መሆኑን አመልክተዋል።

በዚህ መሃል ግን በነዳጅ ዕጥረት ሳቢያ ባለአሽከርካሪዎች ለከፍተኛ እንግልት፣ ትራንስፖርት ተጠቃሚው ሰፊ ህብረተሰብም ለችግር ተዳርገዋል።

በመንግስት በኩል ችግሩን በሚመለከት የተሰጠው መግለጫ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንደሌለና እጥረቱ እንዲፈጠር ያደረጉት አከፋፋዮች ስለመሆናቸው ይገልፃል። በሌላ በኩል  አከፋፋዮቹ ደግሞ “መንግስት ለነዳጅ አቅርቦት የሚያደርገውን ድጎማ ሙሉ በሙሉ ሲያቋርጥ በነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይ የ8 ብር ጭማሪ ማድረግ ነበረበት። የተጨመረው 5 ብር ብቻ መሆኑ ደግሞ ቀሪውን ዕዳ አሸክሞ ለከፍተኛ ዳርጎናል” ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

አሁን በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ተከስቶ የሚገኝ ሲሆን፣ በየማደያዎችም ረጃጅም የተሽከርካሪ ወረፋዎችን ማየት የተለመደ ሆኗል። በአንዳንድ የክልል ከተሞች አንድ ሊትር ነዳጅ በጥቁር ገበያ እስከ 70 ብር በሚደርስ ዋጋ አየተሸጠ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

LEAVE A REPLY