የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ነፃነት መዳፈሩ ተገለጸ

የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ነፃነት መዳፈሩ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የተባበሩት መንግስታት ፀጥታው ም/ቤት በትግራይ የተጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ አጀንዳ አድርጎ ለመወያየት መወሰኑ፣ የአገርን ነፃነትና ሉዓላዊነት ከመዳፈር ተነጥሎ እንደማይታይ መንግስት አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ “ትናንት ሱዳን ግልፅ ወረራ ስትፈፅምብን ምንም ያላደረገውና ራሷ ወረራ ስለማድረጓ መናገሯን ከቁብ ያላለው ኃይል፣ የውስጥ ጉዳያችን በሆነው ህግ የማስከበር ሂደት ገብቶ ለመወያየት መወሰኑን በፀና ተቃውመዋል።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለውና ሉአላዊነትን መዳፈር ነው” በማለትም ዲና ሙፍቲ ድርጊቱን አውግዘዋል።

የተባበሩት መንግስታት ፀጥታው ም/ቤት በትግራይ የተጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ አጀንዳ አድርጎ ለመወያየት ለነገ መጋቢት 1/2013 ቀጠሮ መያዙ ታውቋል።

LEAVE A REPLY