ከባንክ ውጭ የሚያዘው የገንዘብ መጠን በድጋሚ ዝቅ ተደረገ!!

ከባንክ ውጭ የሚያዘው የገንዘብ መጠን በድጋሚ ዝቅ ተደረገ!!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ብሔራዊ ባንክ ከየካቲት 29 ጀምሮ ከባንክ ውጭ የሚያዝ የገንዘብ መጠንንና መሰል ጉዳዮችን የያዙ መመሪዎች ላይ ማሻሻያ አደረገ።

በማሻሻያው መሰረት ከባንክ ውጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለው የገንዘብ መጠን ለድርጅቶች ወደ 200,000 ብር እንዲሁም ለግለሰቦች ወደ 100,000 ብር ዝቅ እንዲል መደረጉን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ገደብ የሚጥል መመሪያ ሲያወጣ በስድስት ወራት ዉስጥ ለ2ተኛ ጊዜ ሲሆን ከስድስት ወራት በፊት የወጣውና እስካሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆየዉ መመሪያ ከባንክ ውጭ ሊኖር የሚችለው የገንዘብ መጠን 1.5 ሚሊዮን ብር የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የባንኩ ምክትል ገዥና ችፍ ኢኮኖሚስት ፍቃዱ ደግፌ መጀመሪያውኑም ተመሳሳይ ገደብ አለመጣል የትም ዓለም የሌለና አግባብነት ያልነበረው አሰራር ነዉ፤ ገንዘቡ የሀገር ሀብት ስለሆነ ባንክ ውስጥ ገብቶ እየተንቀሳቀሰ ጥቅም ላይ መዋል አለበት ሲሉ የማሻሻያውን አስፈላጊነትና ምክንያት ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY