በማይካድራ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ሌላ የጅምላ መቃብር መገኘቱን ዘነኘው የሚድያ ተቋም...

በማይካድራ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ሌላ የጅምላ መቃብር መገኘቱን ዘነኘው የሚድያ ተቋም አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በዓለም ዝነኛና ተዓማኒ ከሆኑ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው ጌቲኢሜጅስ |gettyimages| በማይካድራ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ንጹሀን ተገድለው የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር መገኘቱን አስታወቀ።

በማይካድራ በህወሓት የተገደሉት ሟቾች ቁጥርም ከ1300 እንደበለጠ የከተማዋ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።

ጌቲኢሜጅስ የማይካድራ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ቸሩ ሀጎስን፣ የቀበሌ 01 ሊቀመንበሩ አቶ አብሪሁ ፋንታሁንን እና የከተማዋን ነዋሪዎች ጠቅሶ በምስል ባሰራጨው መረጃ፣ ማርች 5/2020 በአቡነ አረጋዊ ቤተክርሲቲያን የጅምላ መቃብር ውስጥ ከ1300 በላይ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ይፋ አድርጓል።

የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት እነዚሁ ሟቾች ህወሓት ሳምሪ በሚል ባደራጃቸው ወጣቶች፣ ሚሊሻዎች እና በፖሊሶች አማካኝነት የተገደሉ መሆኑን አያይዞ የጠቀሰው በዓለም አቀፍ ታዋቂው ሚዲያ ጌቲኢሜጅስ፤ ሟቾቹ በአካባቢው ላሉ ባለሀብቶች በጉልበት ስራ ተቀጥረው የሚሰሩ ንጹሀን ዜጎች መሆናቸውንና  ገዳዮቹ ቤት ለቤት እየሄዱ የአማራ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ ጭፍጨፋውን መፈጸማቸውን ገልጿል።

LEAVE A REPLY