ጆ ባይደን የትግራይ ጉዳይ ‘’እጅግ እንደሚያሳስባቸው’’ ተገለፀ

ጆ ባይደን የትግራይ ጉዳይ ‘’እጅግ እንደሚያሳስባቸው’’ ተገለፀ

WILMINGTON, DELAWARE - JULY 14: Democratic presidential candidate former Vice President Joe Biden speaks at the Chase Center July 14, 2020 in Wilmington, Delaware. Biden delivered remarks on his campaign's 'Build Back Better' clean energy economic plan. (Photo by Chip Somodevilla/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ቃለ አቀባይ የሆኑት ጄን ሳኪ ለጋዜጠኞች በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ ነው ይሀንን የተናገሩት።

ከትግራይ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ልትወስድ ስለምትችለው ተጨማሪ እርምጃ ከጋዜጠኛ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ አሜሪካ በዲፕሎማቶቿ አማካኝነት እስካሁን የሔደችውን ርቀት አንስተዋል።

በትግራይ ያለው ሁኔታ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ‘’እጅግ ያሳስባቸዋል፤ በቅርበትም እየተከታተሉት ነው” ብለዋል።

“የባይደን አስተዳደር በክልሉ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ እንዲሻሻል የእርዳታ ሰራተኞችን ወደ ክልሉ እንዲገቡ ከማድረግ በተጨማሪ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ ነው” ሲሉም ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY