ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የግብፁ ፅንፈኛ አክቲቪስት ዶክተር ሒሻም ሄግ ማርች 14 በሚከበረው የአለም ወንዞች ቀን የህዳሴ ግድቡ እንዳይሞላ በበዓሉ ወቅት አለማቀፍ ዘመቻ ለማድረግ ደጋፊዎቹን እየመዘገበ ይገኛል።
International Day of Action for Rivers, የሚባለው አመታዊ በዓል የግድቦች ተፅዕኖ ወንዞችን ስለሚጎዳ no Dam for rivers የሚል ቅስቀሳ የሚደረግበት ቀን ነው።
“Rights of Rivers” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የዘንድሮውን አለማቀፍ በዓል፣ ግብፆች የኢትዮጵያ ህልውና የሆነው ግድብ እንዳይሞላ ለሚያደርግ ዘመቻ ተጠቅመውበታል።