*የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 5 ሚሊዮን ብር ለገሰ!
ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ዝነኛው ከያኒ ቴዲ አፍሮና ባለቤቱ፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ ባለሀብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት፤ የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በርካቶች ድጋፍ እያረጉ ባሉበት መርሐ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2 ሚሊዮን፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማዕከሉ ያበረከቱ ሲሆን፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም የ1 ወር ደመወዛቸውን ለግሰዋል፡፡
የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል በቅርስነት የተመዘገበውን የከንቲባ ቢትወደድ ሃይለጊዮርጊስ ወልደሚካኤልን መኖሪያ ቤት ጠብቆ ከማቆየት ባለፈ ወጣቶችን ለማፍራት እንደሚረዳ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
በአሜሪካ የጣይቱ ማእከል መሥራች የሆነቸው አርቲስት እና ገጣሚ ዓለምፀሃይ ወዳጆ ለማዕከሉ መሳካት ከፈተኛ አሰተዋፆ ማበርከቷ ተመልክቷል።