ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጭኮ ከተማ አስተዳደር እና በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ በግለሰቦች ቤት ተከማችቶ የነበረ በርካታ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፌደራል ፓሊስ አስታወቀ።
የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት አቶ ጎሳዬ ለገሰ ዛሬ በሰጡት መገለጫ ፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ለረጅም ጊዜ ሲከታተል ቆይቶ መጋቢት 5 ቀን 2013 ባካሄደው ዘመቻ በጭኮ ከተማ 30 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና ሁለት መትረየስ፣ በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ ፋራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ወልደ አማኑኤል ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ደግሞ 98 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከ4,583 መሰል ጥይት ጋር እዲሁም 3,546 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ከሶስት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡