ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶ የነበረውና የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴን ለከፍተኛ ፈተናና ጫና ዳርጎ የቆየው “በአክሱም የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል በሚል የተሰራጨው የምስል መረጃ” ሀሰተኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ ዘ ስታር አስታውቋል።
በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ “የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል” በሚል በፌስቡክና መሰል ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው የምስል ዘገባ ውሸት መሆኑን በመጥቀስ የምስሉን ትክክለኛ መገኛና ምንጭ በዘገባው ያጋለጠው ዘ ስታር፣ ምስሉ በናይጄሪያ ቦኮሃራም እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2020 የተገደሉ ሰዎች አስከሬን መሆኑን አረጋግጧል።