ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– መጅዲ ኸሊል የተባለው የታወቀ ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ “የግብፅ ጦር የሰበሰበው መሳሪያ በኢትዮጵያ ሰራዊት ፊት ምንም ነው ከማለቱም በላይ በ15 ብረት ለበስ የታጨቀን የግብፅን ጦር አንድ እግረኛ የኢትዮጵያ ወታደር ሁሉንም ማውደም የሚያስችል አቅም ያለው ነው” ሲል ከአልጀዚራ ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሯል።
ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ በግብፅና ኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት በሚመለከት ከቴሌቭዥን ጣቢያው ጋር ቆይታ ያደረገው የፖለቲካ ተንታኙ መጅዲ ኸሊል “በሁሉም የውጊያ ስልት የግብፅ ጦር አንድ ለአስር እንኳን ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር ፊትለፊት መታኮስ አይችልም። የኢትዮጵያ እግረኛ ጦር አይደለም በራሱ ምድር ላይ የሚገኝን ግድብ ማስጠበቅ ይቅርና ከፈለገ በእግር ብቻ እየተዋጋ በ3 ቀን ውስጥ ሱዳንን አልፎ ካይሮ መግባት ይችላል” በማለት ነው የተናገረው።
ከዚሁ ጋር አያይዞም “የጦርነት ፉከራው ይቅርና የግብፅ ህዝብ በቂ ውሃ ማግኘት የሚችልበትን መፍትሄ በሰላማዊ መንገድ መፈለጉ ይሻላል” በማለት ለሀገሩ ግብፅ መንግስት ምክር ለግሷል።