ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን “በትግራይ 70 በመቶ የጤና ተቋማት ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል”...

ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን “በትግራይ 70 በመቶ የጤና ተቋማት ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል” አለ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ፌደራል ፖሊስ ህግ የማስከበር ዘመቻ እያካሄዱ በሚገኙበትና በቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ተደጋግሞ በሚነገርለት የትግራይ ክልል ቀድሞ የተሟላ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩ የጤና ተቋማት 70 ከመቶ ያህሉ ከስራ ውጪ መሆናቸውና 30 በመቶ የሚሆኑት ተቋማት ብቻ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

አለም አቀፋዊ ዕውቅና ያለው ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን እንዳስታወቀው ከፈረንጆቹ ታህሳስ 2020 እስከ መጋቢት 2021 ድረስ 1 መቶ 6 ቦታዎችን በክልሉ በመዘዋወር መመልከቱን ገልፆ፣ በዚህም 70 በመቶ የጤና ተቋማት እንደተዘረፉ እና አገልግሎት እንደማይሰጡ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

“የጤና ተቋማቱ አገልግሎት እንዳይሰጡ ሆነ ተብሎ ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ ተዘርፈዋልም።”
ያለው ቡድኑ “የጤና ተቋማቱ አገልግሎት መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ለከፋ ችግር ተዳርጎል” ሲል አስታውቋል።

LEAVE A REPLY