ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በተወዳዳሪነት ተሳታፊ የሆኑትና በተለያየ መልኩ “የምረጡኝ” ቅስቀሳ ዘመቻ እያደረጉ የሚገኙት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ (ባልደራስ) አዲስ የፖለቲካ ትብብር መመስረታቸው ተገለፀ።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ በፖርቲው ይፋዊ የማህበራዊ ግንኙነት ገፁ በኩል “ለሁሉም ሚዲያዎች” በሚል ባስተላለፈው መልዕክት ” የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ (ባልደራስ) ነገ ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ላይ በራስ አምባ ሆቴል ስለመሰረቱት ፖለቲካዊ ትብብር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ። ስለሆነም የአገራችንና የዓለምአቀፍ የመገናኛ ብዙኃን አካላት በቦታው በመገኘት ጋዜጣዊ መግለጫውን የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡልን በአክብሮት እንጋብዛለን” ሲል ጥሪ አቅርቧል።
ሁለቱ ፖርቲዎች መሠረትን ባሉት የፖለቲካ ዙሪያ ዝርዝር ዘገባውን ነገ ከጋራ መግለጫቸው በኋላ ይዘን እንቀርባለን።