ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሀ እና አቶ ዓለማየሁ ገለታ ዛሬ መጋቢት13/2013 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል ሰጥተዋል።
ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ ኢብሳ ገመዳ ለመገናኛ ብዙሀን እንደገለፁት፣ ተከሳሾቹ በቀረበባቸው ክስ ጥፋት አንደሌለባቸው ለፍርድ ቤት የተናገሩ ሲሆን፣
በአቶ ጀዋር ላይ ከቀረቡት ክሶች አንዱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አባቶች (አምስት ጳጳሶች እና ሁለት አገልጋዮች) እንዲገደሉ ማስተባበር የሚል መሆኑም ተመልክቷል።
አቶ ጃዋር ቤተሰቦቻቸው የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ መሆኑን ጠቅሰው “በሃይማኖት አባቶች ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚያስችላቸው ሁኔታ አንደሌለ” መናገራቸውንም አቶ ኢብሳ ገመዳ ገልፀዋል