ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአውሮፓ ህብረት (EU) በሜ/ጄነራል አብርሃ ካሳ በሚመራው የኤርትራ ብሔራዊ ደህንነት ቢሮ (ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ) ላይ ማዕቀብ ጥሏል። ማዕቀቡ የጉዞ እገዳ እንዲሁም የሀብት/ገንዘብ እገዳን ይጨምራል።
አውሮፓ ህብረት ማዕቀቡን የጣለው በኤርትራ ውስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን፣ በተለይም የዘፈቀደ እስራት ፣ ያለፍርድ ግድያ፣ የሰዎችን ደብዛ በማጥፋት እና በማሰቃየት ምክንያት ነው
በተጨማሪም ህብረቱ ከሩስያ፣ ቻይና ፣ ሰሜን ኮሪያ ፣ ሊቢያ ፣ ደቡብ ሱዳን ግለሰቦች ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ማዕቀብ ጥሏል። እንዲሁም ከማይናማር መፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘ 11 ግለሰቦች ላይ ዕቀብ ተጥሏል።