በአዲስ አበባ የማኅበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባ ሊያካሂድ ነው!

በአዲስ አበባ የማኅበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባ ሊያካሂድ ነው!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበአዲስ አበባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በማህበር ተደራጅተው ቤት መስራት የለሚፈልጉ ዜጎች ምዝገባ እንደሚጀመር የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ኤጀንሲ አስታወቀ።

በምዝገባው ተጠቃሚ የሚሆኑት በ2005 በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት መርሐ ግብር ተመዝግበው ቤት ለማግኘት የሚጠባበቁት ብቻ መሆናቸውን ያስታወቀው ኤጀንሲው፣ ምዝገባውን በኦንላይን እንደሚከናውንም አመልክቷል።

እንደ ኤጀንሲው መግለጫ ከሆነ፣ በማህበር የተደራጁ የመርሐ ግብሩ ተጠቃሚዎች እጣ ከወጣላቸው የቤት ግንባታ ወጪውን 70 በመቶ በባንክ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

30 በመቶ ሴት ተመዝጋቢዎች እንዲሁም 20 በመቶ የመንግስት ሰራተኞች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ተብሏል።
በመርሐ ግብሩ በ2005 ተመዝግበው ቁጠባ ያቋረጡ በማህበር ቤት ልማቱ ሊመዘገቡ አይችሉም ተብሏል።

LEAVE A REPLY