ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የምርጫ ማኒፌስቶውን ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።
የቃልኪዳን ሰነዱን ለማዘጋጀት ላለፉት 2 ዓመታት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደነበር የገለጸው ፓርቲው፣ “ሰነዱ በሀገር ደህንነት እንዲሁም በፓለቲካ፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ያሉ መሰረታዊ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በግልፅ ያስቀመጠ” መሆኑን አመልክቷል።
ፓርቲው በመጪው ምርጫ ለአሸናፊነት የሚያበቃ የህዝብ ድምፅ አግኝቶ አገር ለማስተዳደር ቢመረጥ፣ ለቀጣይ 5 ዓመታት በስራ ላይ የሚውል እና የገባውን ቃል ካልተገበረ ተጠያቂ የሚሆንበትን ሰነድ ማዘጋጀቱንም የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።