ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አሁን ኢትዮጵያን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ብልፅግና እና ተቃዋሚው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) በመጪው አገራዊ ምርጫ በጋራ ለመወዳደር ያስችለናል ያሉትን ቅንጅት መመስረታቸውን አስታወቁ።
የፓርቲዎቹ አመራር ዛሬ በሀዋሳ በሰጡት የጋራ መግለጫ እንዳሉት፣ የፊታችን ግንቦት ወር ሊካሄድ በታቀደው 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ በጥምረት ለመወዳደር የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈፀማቸውን በይፋ ገልጸዋል።