የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ8 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ ተቃርቧል!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ8 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ ተቃርቧል!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዋልያዎቹ ትናንት የማዳጋስካር አቻቸውን ያሸነፉበት አመርቂ ውጤትና በጨዋታው ያሳዩት ድንቅ አቋምና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴው፣ ኢትዮጵያ ከስምንት ዓመት በኋላ ወደመሰረተችው የአፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ መቃረቧን አመላካች ነው ተብሏል።

ለአገር ቤትና ለውጭ አገራት ዓለም አቀፍ የስፖርት ሚዲያዎች የሚሰሩ የእግር ኳስ ተንታኞች ከትናንቱ የ4ለ0 ድል በኋላ ደጋግመው ሲናገሩ እንደተደመጠው ከሆነ፣ ዋልያዎቹ በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በግልና በቡድን ካሳዩት ድንቅ አቋምና ብቃት አንፃር የተገኘው ውጤት የሚያንስ እንጂ የሚበዛ እንዳልሆነ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ከኮትዲቫር አቻው ጋር በሚያደርገው ጨዋታ አቻ መውጣት የሚችል ከሆነ ከ8 አመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለሱን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ አሁን ባለው ነጥብም ምድቡን በአንደኝነት እየመራ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰላምና አጠቃላይ የኑሮ ሁኔታ ህዝቡን ለከፋ ሀዘንና “ድብርት” ዳርጎ በሚገኝበት ወቅት እንደዚህ ያሉ የድል ዜናዎች መሰማታቸው፣ የህዝብን ስሜት በማነቃቃትና አንድነትን በማጠናከር በኩል ያላቸው ፋይዳም ከፍተኛ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል።

ዋልያዎቹ ቀጣዩ ጨዋታ ተፈላጊውን ውጤት የሚያስመዘግቡበትና ሀገራቸውን የሚያኮሩበት እንዲሆን ከወዲሁ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።

LEAVE A REPLY