ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለስራ ጉብኝት አስመራ መግባታቸውን በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኤንባሲ አስታውቋል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለዶ/ር ዐቢይ እና በእርሳቸው ለተመራው ከፍተኛ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን አቀባበል አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ወደአስመራ ያቀኑበት ዋና ምክንያትና በቆይታቸው ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አጀንዳ አድርገው የሚወያዩባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ባይገለፁም፣ በትግራይ ክልል ከተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ ጋር ተያይዞ በሁለቱ ሀገራት ወታደሮች ተፈፀሙ በተባሉ ግድያና የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ላይ ይመከራሉ ተብሎ ተገምቷል።