ለቀናት ተዘግቶ የቆየው የአዲስ አበባ – ደሴ መንገድ በመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት ስራ...

ለቀናት ተዘግቶ የቆየው የአዲስ አበባ – ደሴ መንገድ በመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት ስራ ጀመረ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየካቲት 10 ቀን 2013 ዓ/ም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና ልዩ ቦታው አጣዬ ከተማ እና ዙሪያ ባሉ የኦሮሞ ብሄረሰብ አሰተዳደር ዞን አካባቢዎች ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ ከአገልግሎት ውጪ ዝግ ሆኖ የቆየው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚያስኬደው ዋናው መንገድ ተከፍቷል።

ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ነገ ገልፀዋል።

እንደ አካባቢው ነዋሪዎች ከሆነ፣ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ቢጀመርምና በአጣዬ፣ ጀውሃ፣ በካራቆሪ፣ በማጀቴ፣ በከሚሴና በሸዋሮቢት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም፣ አሁንም ግን ግጭቱ መልሶ ሊከሰት ይችላል የሚለው የነዋሪዎች ስጋት ከፍተኛ ነው።

በሰሜን ሸዋ ዞን በርካታ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት የበርካቶችን ህይወት ስለማለፉና እስካሁን ግምቱ ያልታወቀ ከፍተኛ ንብረት ስለመውደሙ በተከታታይ መዘገባችን ይታወሳል።

LEAVE A REPLY