ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ድምፃዊ ጌታቸው ጋዲሳ “የቁርጥ ቀን ልጅ ነኝ” እና “የንፁሐን ደም” የተሰኙ ሁለት ነጠላ የሙዚቃ ስራዎቹን ዛሬ መጋቢት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በብሔራዊ ቲያትር አስመረቀ።
“የቁርጥ ቀን ልጅ ነኝ” የተሰኘው ሙዚቃ የመከላከያ ሰራዊትን ተጋድሎ እንዲሁም ትናንትና ዛሬ ለአገሩ ክብርና ሉዓላዊነት የከፈለውን መስዋዕትነት የሚዘክር ሲሆን፣ “የንፁሐን ደም” የተሰኘው ሙዚቃ ደግሞ ዘርን መሰረት ባደረገ ጥቃት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በግፍ የሚገደሉ ዜጎችን በሰማዕትነት የሚዘክር እንደሆነ ታውቋል።
ድምፃዊው ሁለቱን ወቅታዊ ስራዎቹን ዛሬ በብሔራዊ ቲያትር ባስመረቀበት ወቅት እንደተናገረው “የንፁሐን ደም” የተሰኘው ሙዚቃ በተለይም “በሻሸመኔ ተዘቅዝቆ ለተሰቀለው ወጣት መታሰቢያነት የተዘጋጀ ነው።