በርካታ ሰዎችን የበላው አዞ መገደልና ለገዳዩ ተሰጠ የተባለው ሽልማት አነጋጋሪ ሆኗል!

በርካታ ሰዎችን የበላው አዞ መገደልና ለገዳዩ ተሰጠ የተባለው ሽልማት አነጋጋሪ ሆኗል!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበጋምቤላ ክልል ባሮ ወንዝ ውስጥ በርካታ ሰዎችን እየበላ ሲያስቸግር የነበረውን አዞ በአንድ የአካባቢው ተወላጅ መገደሉ የተገለፀ ሲሆን፣ “ጀግና” ለተባለው የአዞው ገዳይ “20 ከብት እና አንድ ልጃገረድ ተሸለመ” መባሉ የማህበረሰብ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

በባሮ ወንዝ ውስጥ ራሱን ደብቆ ባልታሰበ ጊዜና ሁኔታ በበርካታ ሰዎች ላይ “ጥቃት ሲያደርስ ነበር” የተባለው አዞ፣ ከተገደለ በኋላ የሆድ ዕቃው ሲከፈት አስደንጋጭ እውነት መከሰቱን ታወቀ። በአዞው ሆድ ውስጥ የተለያዩ ጫማዎች እና የሰው የሆኑ ቁሳቁሶች ተገኝተዋል።

ይሁንና፣ ለዚህ አደገኛ አዞ ገዳይ “የ20 ከብት እና አንድ ልጃገረድ ሽልማት ተበረከተለት” መባሉ በበርካታ ዜጎች ዘንድ ዋነኛ መነጋገሪያ ከመሆኑም ባሻገር አንዳንዶችንም ለተቃውሞ ማነሳሳቱን ለመታዘብ ተችሏል።

“አለም በስልጣኔ ወደፊት እየገሰገሰች ባለችበት በዚህ ዘመን ዛሬም ኢትዮጵያ ውስጥ ሴት ልጅ እንደ ዕቃ እየተቆጠረች ነው” የሚሉ የተቃውሞ ሀሳቦችን እያስተናገደ ከሚገኘው የአዞው መገደል ዜና ጋር ተያይዞ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች የተለያየ ሀሳባቸውን እየሰጡበት ይገኛሉ።

LEAVE A REPLY