ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ በመሆን በኮሮና ቫይረስ ስርጭትና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተመለከተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ እድሜያቸዉ ከ65 ዓመት በላይ ለሆናቸው ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም እድሜያቸው 55 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የጎንዮሽ የጤና ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ፈጥነው ሪፖርት ካደረጉ ክትባቱ እንደሚሰጣቸው የገለፁት ሚኒስትሯ፣ በቅርቡ ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባና በአሁኑ ወቅት በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መዘናጋት እንደሚታይ አመልክተው “ይህ ቸልተኝነት ዋጋ እያስከፈለን ነውና የጥንቃቄ እርምጃዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል።