ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሁን ወዳሉበት ሃላፊነት የመጡበትን ሶስተኛ ዓመት አስመልክቶ ነገ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በተሸከርካሪ ሊካሄድ የታቀደው የድጋፍ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አስተባባሪ ኮሚቴው ገለጸ፡፡
ከጤና ሚኒስቴር ጋር በተደረገው ምክክር የኮቪድ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱ ለመራዘሙ ምክንያት መሆኑን ከአስተባባሪ ኮሚቴው መካከል አቶ ሞቲ ሞሮዳ ገለፀዋል። በተሽከርካሪ የድጋፍ ሰልፍ በሚካሄድበት ወቅትና የተሸከርካሪ ድምጽ በሚሰማበት ጊዜ ህብረተሰቡ ወደ መንገድ መውጣቱና መሰብሰቡ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ ለስርጭቱ መስፋፋት የበኩሉን ድርሻ ሊያበረክት ይችላል በሚል ጤና ሚኒስቴር ስጋቱን በመግለጹ የድጋፍ ሰልፉን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ወስነናል” ብለዋል፡፡