ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የክልሉ ዋና ከተማ የሆነችው መቀሌን ጨምሮ በአብዛኞቹ የትግራይ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተነገረ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞገስ መኮንን በአብዛኞቹ የትግራይ ክልል ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን አረጋግጠው “ይሁንና የተቋረጠበት ቦታ ተለይቶ ያጋጠመውን ችግር መለየት እስኪቻል ድረስ ምክንያቱ ይሄ ነው ብሎ መግለፅ አይቻልም” ብለዋል።
“ትክክለኛ ቦታውን የመለየት ስራ ተጀምሯል” ያሉት አቶ ሞገስ “ኤሌክትሪክ በተቋረጠባቸው ከተሞች ኤሌክትሪክ የሚመለሰው ችግሩ ተለይቶ አስቸኳይ የጥገና ስራ እንደተጠናቀቀ ነው” ሲሉም አስታውቀዋል።
የትሕነግ ኃይል ህግ የማስከበር ዘመቻ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ወቅት ትልልቅ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮችን የመቁረጥና ህዝቡ ምሬት ውስጥ እንዲገባ የማድረግ ስልት እንደሚጠቀም ተደጋግሞ ሲገለፅ መቆየቱ ይታወቃል።