ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከኢትዮጵያውያን እናትና አባት በካናዳ የተወለደውና የጥላሁን ገሠሠና የአስቴር አወቀ ሙዚቃዎችን እየሰማ እንዳደገ ደጋግሞ የሚናገረው ዓለም አቀፍ ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ)፣ በትግራይ ክልል ለሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲውል 1 ሚሊየን ዶላር መስጠቱን የአለም ምግብ ፕሮግራም(WFP) አስታውቋል።
የአቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) ድጋፍ፣ የአለም ምግብ ፕሮግራም በመጪው ስድስት ወራት የአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት እንደሚያግዝ ያስታወቁት በአሜሪካ የአለም ምግብ ፕሮግራም ፕሬዝዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ባሮን ሴጋር “ዘ ዊኬንድ አሁን በትግራይ ክልል የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ እንዲቻል የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ በማድረጉ የአለም ምግብ ፕሮግራም የተለየ ዕውቅና ይሰጠዋል” በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘ ዊኬንድ ከዚህ ቀደም በረሃብ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበርም የአለም ምግብ ፕሮግራም በድረ ገፁ አመልክቷል።