ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ እና ጓደኞቹ የተመሰረተው ህብረት ለበጎ የተሰኘው የበጎ አድራጎት ማህበር ከያዛቸው በርካታ ህልሞች መሀል ዋነኛ የሆነውን ሆስፒታል የማስገንባት ህልም እውን ለማድረግ ይረዳው ዘንድ የለገጣፎ ከተማ አስተዳደር 6000 ካሬ ሜትር ቦታ ለማህበሩ ለመስጠት ማዘጋጀቱ ተሰምቷል።
የዚህን መሬት ርክክብ እና የሆስፒታሉን መሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ መርሀግብር ነገ መጋቢት 28 በለገጣፎ ከተማ እንደሚካሄድም ለኢትዮጵያ ነገ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።