የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ12 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ12 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሚመለከታቸው የትምህርት ክፍሎች ተመርመሮ፣ በየኮሌጆች አካዳሚክ ጉባዔዎች ተፈትሾ፣ ተገመግሞና በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ በቀረበለት መረጃ መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ የ12 ምሁራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዳፀደቀ በድረ ገፁ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፤ ኘሮፌሰር ይልማ ስለሺ (የሲቪል እና ኢንቫይሮመንታል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር አለሙ መኮንን (የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር አለማየሁ ገዳ (የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር በርሲሳ ኩምሳ ይልማ ስለሺ (የፓቶሎጂና ፓራሲቶሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር ገበየሁ ጎሹ (የእንስሳት ህክምናና ግብርና ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር ሙሉጌታ አጥናፉ (የሳይንስና ሒሳብ ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር ጌታቸው ተረፈ ( (የፓቶሎጂና ፓራሲቶሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር አሰፋ ፍሰሀ (የፌደራሊስትና አስተዳደር ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር ንጋቱ ከበደ (የፓቶባዮሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር ግርማ ዘርአዮሐንስ (የኢንቫይሮመንታል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር ሽመልስ አድማሱ (የኬሚካልና ባዮኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል ባልደረባ)፣ ኘሮፌሰር አታላይ አየለ (የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ትምህርት ክፍል ባልደረባ) የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል።

LEAVE A REPLY