ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– “በአሁኑ ሰዓት ህወሐት ሞቷል፤ ለሁከትና ብጥብጥ ይጠቀምበት የነበረውን ኢኮኖሚም አጥቷል፤ የሚያስተዳድረው ህዝብ ባለመኖሩ የትግራይ ህዝብ ከአፈና ነፃ ወጥቷል፤ ግዳጅ ሰጪም ሆነ ተቀብሎ የሚፈፅም መዋቅርም የለውም” ሲሉ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ተናግረዋል።
ጄነራሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ “በጣም ህይወታቸውን የሚወዱ፣ የፎከሩትን ያህል ለትግራይ ህዝብ ያልሰሩትን ከሀዲ ጁንታዎች ጀግናው ሠራዊታችን ከየተወሸቁበት እያወጣ መሰባበሩን ቀጥሎበታል። እብሪተኛው የጁንታ ኃይል ሙሉ በሙሉ ከተደመሰሰ በኋላ ሠራዊታችን የተራረፉትንና በየጫካው የተበተኑትን በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን በማደን ለህግ የማቅረብ ዘመቻውን ቀጥሏል፤ በርካታ ድሎችም አስመዝግቧል” ብለዋል።
“ከሃዲው ለሁከትና ብጥብጥ ያከማቸውና የዘረፈው ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ በሰራዊታችን ቁጥጥር ስር ገብቷል። የሰው ኃይሉም ተደምስሷል፣ ተማርኳል፤ የተወሰኑት ፅንፈኞችም በትግራይ በረሃ ህይወታቸውን ለማትረፍ እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ” ሲሉ አስታውቀዋ።