በመጋቢት ወር 22 ከመቶ የምግብ ዋጋ ግሽበት መመዝገቡን ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ!

በመጋቢት ወር 22 ከመቶ የምግብ ዋጋ ግሽበት መመዝገቡን ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በቀደሙት ወራት በእህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው መጋቢት ወርም የቀጠለ መሆኑን የገለፀው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ፣ የመጋቢት ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ22 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቋል።

“የምግብ ዘይት፣ የቅመማ ቅመም፣ የበርበሬ፣ የፍራፍሬ፣ የአትክልትና የቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህ ወርም በመቀጠሉ የዋጋ ግሽበት ምጣኔው ጭማሪ አሳይቷል” ሲል ኤጀንሲው አስታወቋል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት የመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18 ነጥብ 9 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ፈጣን ዕድገት ማሳየቱንና የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ፣ ልብስና ጫማ፣ አነቃቂዎች፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት መስሪያ እቃዎች (ሲሚንቶና የቤት ክዳን ቆርቆሮ)፣ ህክምና፣ ትራንስፖርት (ነዳጅ) እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ መሆኑን አመልክቷል፡፡

LEAVE A REPLY