ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ “የፍቅር፣የ መተሳሰብ እና የመተዛዘን” ጥሪ አቀረቡ!

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ “የፍቅር፣የ መተሳሰብ እና የመተዛዘን” ጥሪ አቀረቡ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ፣ መጪውን የረመዳን ቅዱስ ወር አስመልክተው በሰጡት መግለጫ “ረመዳን ጾም የበረካ ወር በመሆኑ በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመተዛዘን ማሳለፍ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚሁ የዛሬ መግለጫቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች እየተከሰተ ያለው የሰዎች ግድያ መቆም እንዳለበት ያሳሰቡት ተቀዳሚ ሙፍቲ፣ የሃይማኖት አባቶች በመተባበር ሕዝቡን ማስተማር እንደሚገባቸውና መንግሥትም ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

“ለአገራችን አንድነት እና ለህዝባችን ሠላም ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት” ሲሉ ያሳሰቡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንቱ፣ “በጾሙ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ታሳቢ ያደረገ ጥንቃቄ እናድርግ። ከወንጀል እና ከበደል በመቆጠብም ወደአምላክ እንቅረብ፤ ከአምላክ ጋር እንታረቅ” ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY